አሜሪካ እና ኢራን ለስምምነት “የመጨረሻው ጣር” ላይ እንደሆኑ ትራምፕ ተናገሩ
አሜሪካ እና ኢራን የስምምነት “የመጨረሻው ጣር” ላይ እንደሆኑ እና ስምምነቱ “በማንኛውም መንገድ፣ ቅርጽ ወይም ሁኔታ የኒውክሌር መሣሪያን እንደማይፈቅድ” ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ካደረጉ በኋላ በነበሩ የተለያዩ የግጭቱ ምዕራፎች ወቅት ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን የሚጠቁም አስተያየት መስጠታቸው ይታወሳል።
በጄኤፍኬ አውሮፕላን ማረፊያ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ስምምነቱ “በጣም ድንቅ ይሆናል” ብለዋል።
ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንደማይኖራት በድጋሚ ያስረገጡት ትራምፕ፤ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የሆርሙዝ ወሽመጥ “በአፋጣኝ እንደሚከፈት” ጠቁመዋል።
“በሁለት ወይም በሦስት ቀናት ውስጥ” የሆርሙዝ ወሽመጥ ሊከፈት እንደሚችልም ተናግረዋል።
ኢራን እና እስራኤል አንዳቸው ሌላቸው ላይ ጥቃት ማድረስ ለማቆም መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ትራምፕ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ካነጋገሩ በኋላ ኢራን ላይ ጥቃት ማድረስ ለማቆም መስማማታቸውን ተናግረዋል።
“ለተጨማሪ አንድ ሳምንት ገደማ አይተነኳኮሱም” ሲሉም አክለዋል።